top of page
299039089_5352544118155564_7191751842538420446_n.jpg

Our Story

Rehoboth Grace Ethiopian Evangelical Church is a community of faith rooted in the love of God. We believe worship is not just found in prayer, it’s something expressed in everything we do. Our philosophy is deeply rooted in the Holy Scriptures, life’s only guidebook. Come and join us to experience God’s grace for yourself. There’s a special place for you at our church in Malden.

Our Calling

At Rehoboth Grace Ethiopian Evangelical church, we pursue the Glory of God through worship, ministry, giving and education. We strive to connect with Jesus Christ and to each other, in order to magnify His name. At the heart of everything we do is the understanding that we must love God with all our heart, with all our soul and with all our mind.

website.pic.1rgeec.jpg
293032324_5257195634357080_1961148408230687360_n.jpg

​የሮሆቦት የፀጋ ወንጌል ቤተክርስቲያን አመሰራረት

ሮሆቦት የፀጋ ወንጌል ቤተክርስቲያን በአሜሪካ ማሳቹሴት ስቴት ሞልደን ከተማ በ2014 ጁን ወር ላይ በእግዚአብሔር ቀጥተኛ ምሪት እና ፀጋ ተመሥርታለች። በጥቂት ቅዱሳን ስብስብ የተጀመረች ይህች ቤተክርስቲያን “ጅማሬህም ታናሽ ቢሆንም እንኳ ፍፃሜህ እጅግ ይበዛል”(ኢዮ.8:7) ተብሎ በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ እንደተጠቀሰው እየበዛች እየሰፋች እያደገች መጥታለች ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።

 

 

የሮሆቦት የፀጋ ወንጌል ቤተክርስቲያን መመሪያ

የእግዚአብሔር ሥራ እያደገ በሚሄድባት የክርስቶስ አካል ደግሞ ነገሮች በሥረዓት እንዲሔዱ መመሪያን እና ውስጠ ደንቦችን ማውጣት አስፈላጊ መሆኑ ከቤተክርስቲያን አጀማመር፤ ታሪክና ዕድገት እንማራለን። ቤተክርስቲያን የምትመራው በእግዚአብሔር ቃልና በመንፈስ ቅዱስ ነው። እነዚህን ሁለቱን ዋና መመሪያዎቿን ተመርኩዛ በሥሩ ደንቦችን ማውጣት ግዴታ ሆኗል። ቤተክርስቲያናችን ታቅፋ በምትገኝበት ዲኖሚነሽን በአሰምብሊስ ኦፍ ጎድ  (Denomination Assembly of God) ዋናውን መተዳደሪያ ደንብ ላይ በመመርኮዝ የኢቲዮጵያውያውንና ኤርትራውያን ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናትንም ደንቦችንና ልምምዶችን ያካተተ ደንብ (Bylaws) አውጥታለች። ይህ ደንብ ለጅማሬ ያክል እንዲረዳ ተብሎ የተሠራ በመሆኑ በስፋት ብዙ ነገሮን አላካተተም። ለምሣሌ በኤፌሶን መዕራፍ አራት ላይ የተጠቀሱቱን ከአምስቱ የአገልግሎት ቢሮዎች ሁለቱን (ማለትም እርኞችንና ወንጌላውያንን ብቻ) አካቶአል። ሌሎች የቀሩት ሐዋሪያት፤ ነቢያትና አስተማሪዎችን ለወደፊት ከቤክርስቲያኒቷ ዕድገት ጋር ተያይዞ እንደሚሠራ ይታሰባል።

bottom of page